አስቸኳይ አዋጁን ሲያፈጽሙ የነበሩ ሁለት የራያ፣ ቆቦ ወረዳ አመራርች ተገደሉ

አስቸኳይ አዋጁን ሲያፈጽሙ የነበሩ ሁለት የራያ፣ ቆቦ ወረዳ አመራርች ተገደሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት የራያ ቆቦ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በተፈጸመባቸው ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ።

የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪና የወረዳው የሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ሓላፊ የሆኑት ሁለቱ ግለሰቦች አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ወቅት በተፈጸመባቸው ጥቃት ሕይወታቸው እንዳጡ የሰሜን ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያም አረጋግጧል።
ሁለቱ የሥራ ሓላፊዎች ጥቃቱ የተፈጸመባቸው በወረዳ 08 ቀበሌ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከለውን ሰርግ ለማድረግ የተዘጋጁ ሰዎችን ድርጊት ለማስቆም ከደጋሾቹ ጋር ተነጋግረው ሲመለሱ እንደሆነ የመምሪያ ሓላፊው አቶ አሳዬ ተገኘ ተናግረዋል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስዩም መስፍንና የወረዳው የሰላምና ደህንነት ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ መንገሻ ሞላ በመንገድ ላይ ሳሉ የሰርጉ ታዳሚዎች በአንድ ባጃጅ በብዛት መሳፈራቸውን በማየታቸው፣ አሽከርካሪውን አስቁመው ሲያናግሩ ከተሳፋሪዎች በተተኮሰ ጥይት የሁለቱም አመራሮች ሕይወት እንዳለፈ ታውቋል።
ትናንት ከሰዐት በኋላ ከራያ ቆቦ ወረዳ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ 08 ቀበሌ ልዩ ስሙ” አራዶ” ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ላይ ወንጀሉን የፈጸሙት ተጠርጣሪዎች ታርጋ በሌለው ሌላ ባጃጅ ተሳፍረው ከአካባቢው ለገዜው የተሰወሩ ቢሆንም፤ የዞኑ እና የወረዳው የጸጥታ ኃይሎችም በጋራ በመሆን የወንጀሉን ፈጻሚዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ ለማቅረብ የተጠናከረ የክትትልና የአሰሳ ሥራ እያካሄዱ ነው ተብሏል።

LEAVE A REPLY