የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወርሃዊ ወጪውን ኢኮኖሚው ድጎማ እያደረገ ነው ተባለ 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወርሃዊ ወጪውን ኢኮኖሚው ድጎማ እያደረገ ነው ተባለ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኮሮና ቫይረስ ዓለም ዐቀፍ ቢዝነሶች ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ በእጅጉ መቋቋሙ የሚነገርተለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ120 ሚሊየን ዶላር በላይ በማስገባት ወርሃዊ ወጪዬን ሸፍኜ የሀገሪቱንም ኢኮኖሚ እየደገፍኩ ነው አለ።

አየር መንገዱ ፈጥኖ አማራጭ መንገድን በመመልከት ወደ ካርጎ አገልግሎት መግባቱ  ውጤታማ አድርጎታል ያሉት የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም፤ “ኮቪድ- 19 በዓለም ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ በአየር መንገዱ ላይም ተመሣሣይ ጉዳት ቢያደርስበትም፣ በርካታ አየር መንገዶች በድጎማና በብድር ውስጥ በገቡበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ወጪውን ሸፍኖ ለመንግሥት ድጋፍ ለማድረግ በቅቷል” ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁስ የሚተላለፍባት ምቹ ቦታ ተደርጋ መወሰዷ እና አየር መንገዱ በዓለም ገበያ ላይ አበባን ለማጓጓዝ ተመራጭ መሆኑ ለውጤታማነቱ ዓይነተኛ ሚና ተጫውተዋል ነው የተባለዉ።
በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን ከ200 እስከ 300 ቶን አበባ ወደ ተለያዩ አገሮች በማጓጓዝ ፣ በኢትየጵያ ያለውን የአበባ ምርት እንዲበረታታ ከማድረጉ በላይ በውጭ ምንዛሪ ኢኮኖሚውን እየደገፈ ነው የሚሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ በረመዳን ወቅት ሥጋ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በማጓጓዝ ከፍተኛ ገቢ መገኘቱንም ታውቋል።
በዚህ መሠረት አየር መንገዱ ወጪውን ሸፍኖ ለአገሪቱ ኢኮኖሚው ድጋፍ ማድረጉ በዓለም ካሉት አየር መንገዶች ጠንካራ ያስብለዋል በማለት የተቋማቸውን ወቅታዊ አቋም ያመላከቱት አቶ ተወልደ፤ በቀጣይም የዓለም ዐቀፉን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በማየት ተጨማሪ የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ጭነት ማመላለሻነት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

LEAVE A REPLY