የኢንዱስትሪ ፓርኮች 122 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ አስገኝተዋል ተባለ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች 122 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ አስገኝተዋል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢንዱስትሪ ፓርኮች ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት የተሻለ የውጭ ምንዛሪ አስገኝተዋል ተባለ።

በዘጠኝ ወራት 122 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማስገኘታቸውን በኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን – የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሓላፊ ገልፀዋል።
ገቢው አምና በተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው በ32 በመቶ ብልጫ አለው ያሉት የኮሚኒኬሽን ባለሙያው፤ አፈፃፀሙ ከዕቅዱ ጋር ሲመሳከርም 75 በመቶ እንደሆነ አስረድተዋል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተመረቱ በኋላ ወደ ውጪ ተልከው ገቢውን ካስገኙት መካከል ጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ውጤቶች ተልከዋል ተብሏል።
የበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት አፈፃፀም ግን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተፅዕኖ ምክንያት ይቀንሳል የሚል ግምት እንዳለ የጠቆሙት አቶ ደርቤ፤ የዘጠኝ ወራቱ አፈፃፀም ጥሩ የሆነው አብዛኞቹ ጊዜያት የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከመከሰቱ በፊት የነበሩ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
በሀገራችን ካሉ 12 የኢንዱስትሪ ፓርኮች 7ቱ በሥራ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ቀሪዎቹም በቅርብ ጊዜ ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY