የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች እና መምህራን ያለክፍያ በዲጂታል ቤተመጽሐፍት እንዲጠቀሙ  ውሳኔ ተላለፈ

የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች እና መምህራን ያለክፍያ በዲጂታል ቤተመጽሐፍት እንዲጠቀሙ  ውሳኔ ተላለፈ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የከፍተኛ ትምህርትና ሥልጠና ተማሪዎች እና መምህራን ያለክፍያ በዲጂታል ቤተመጽሐፍት እንዲጠቀሙ መወሰኑን ተወሰነ።

ኮቪድ-19 ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ የከፍተኛ ትምህርት እና ሥልጠና (የዩኒቨርስቲዎች እና ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና) በመቋረጡ፣ ትምህርትን በቴክኖሎጂ አስደግፎ በኦንላይን የማስቀጠል ሥራ እየተሠራ ነው ተብሏል።
የተማሪዎችን ኢኮኖሚያዊ አቅምን በመገንዘብ በነፃ መጠቀም ለማስቻል፤ ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በመተባበር ከከፍያ ነፃ  እንዲሆን መወሰኑን ትምህርትን በኦን ላይን ያቀረበው  የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የከፍተኛ ትምህርትና ሥልጠና ማኅበረሰቡ በ http://ndl.ethernet.edu.et/ ገብቶ የነፃ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል የገለፀው ተቋሙ ተማሪዎች እና መምህራን የኦንላይን መማር ማስተማር ሂደቱን በዚሁ አግባቡ እንዲቀጥሉም አሳስቧል።

LEAVE A REPLY