በአማራ ክልል ከ400 ሺኅ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ተጠቅተዋል ተባለ

በአማራ ክልል ከ400 ሺኅ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ተጠቅተዋል ተባለ

Macro Photo of Yellow Fever, Malaria, Dengue or Zika Virus Infected Mosquito Insect Macro on Yellow Background

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት በክልሉ የሚገኙ ከ400 ሺኅ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን አስታወቀ።

በዚህ ዓመት ቁጥራቸው እጅግ የበዛ ሰዎች በወባ ለመጠቃታቸው እና በክልሉ ለተከሰተው የወባ በሽታ ስርጭት መስፋፋት ዋነኛ ምክንያቶች መሀል፤ በኅብረተሰቡ ዘንድ፣ እንዲሁም በመንግሥት ተቋማት የተፈጠረ ትኩረት ማጣት ነው ሲሉ የተናገሩት የኢንስቲትዩቱ የወባ በሽታ የቡድን መሪ አቶ ማስተዋል ወርቁ፤  የተጠቂዎች ቁጥር ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 73 በመቶ መጨመሩንም ገልጸዋል።
በሽታውን በአግባቡ መቆጣጠር ካልተቻለ አሁን ላይ ያለው 400 ሺኅ የወባ ታማሚ በመጪው ክረምት ወራት በእጅጉ ሊጨምር እንደሚችልም ተነግሯል።

LEAVE A REPLY