ተጨማሪ 87 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ ሁለት ሰዎችም ሕይወታቸው አልፏል

ተጨማሪ 87 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ ሁለት ሰዎችም ሕይወታቸው አልፏል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፉት 24 ሰዐታት ለ3 ሺኅ 932 ሰዎች በተደረገ  የላብራቶሪ ምርመራ፣ ተጨማሪ 87 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለፀ።

ይህን ተከትሎ በሀገሪቱ አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 1 ሺኅ 344 መድረሱ ታውቋል።

ዛሬ ቫይረሱ እንደተገኘ የተረጋገጠባቸው ከ10 እስከ 70 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ  59 ወንድና 28 ሴቶች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ ከእነርሱም መሀል 67 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 6 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል እና 7 ሰዎች ከአማራ ክልል እንዲሁም አንድ ሰው ከሐረሪ እና 4 ሶማሌ ክልል ነዋሪዎች ውስጥ መሆናቸውንም ይፋ አድርጓል።
 ቫይረሱ ከተገኘባቸው 87 ሰዎች መካከል 28 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 18 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው፣ እንዲሁም 41 ሰዎች ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው እንደሆኑ ተሰምቷል።
በሌላ በኩል ተጨማሪ 14 ሰዎች (6 ከኦሮሚያ ክልል፣ 8 ከሶማሌ ክልል) ማገገማቸውን ተከትሎ እስካሁን 231 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል ያለው የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር፤ በዛሬው እለት የሁለት ኢትዮጵያውያን ሕይወት በማለፉ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 14 መድረሱን አረጋግጧል።
ቫይረሱ ተገኝቶባቸው 1ሺኅ 97 ሰዎች በለይቶ ሕክምና ውስጥ እንደሚገኙና ስምንት ሰዎች በጽኑ ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነም ታውቋል።

LEAVE A REPLY