የቻይና ኩባንያዎች ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ500 ሺኅ በላይ ማስኮች ድጋፍ አደረጉ

የቻይና ኩባንያዎች ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ500 ሺኅ በላይ ማስኮች ድጋፍ አደረጉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከ6 የቻይና ተቋማት የተሰባሰቡ 500 ሺኅ ማስኮችና የተለያዩ ቁሳቁሶች ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተበረከቱ።

እርዳታውን በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሬ ለምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ዛሬ አስረክበዋል።
በተያያዘ ዜና የተለያዩ ሀገር በቀል ተቋማትም 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፤ በተጨማሪም 180 ሺኅ ብር የሚገመት በእግር የሚሠራ የእጅ መታጠቢያ ድጋፍ መደረጉ ታውቋል።
ዛሬ በድጋፍ የተገኙት 500 ሺኅ ማስኮች ለመንግሥት ሠራተኞች፣ ለጤና ባለሙያዎች እና ለፖሊሶች እንደሚከፋፈሉም ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY