ችግኝ ተከላ አርብ በይፋ እንደሚጀመር ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ

ችግኝ ተከላ አርብ በይፋ እንደሚጀመር ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የፊታችን ዓርብ ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ዓመታዊውን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በይፋ እንጀምራለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጊዜው በሀገሪቱ መፃኢ ዕድል ላይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ክፉ ጥላ ያጠላበት ቢመስልም፤ ከችግሮቻችን ጋር እየታገልንም ቢሆን ያሰብናቸውን ሀገራዊ እቅዶች በሙሉ ለማሳካት እንሠራለን ብለዋል።
“ባለፈው ዓመት እያንዳንዳችን ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለን፣ ያቀድነውን አሳክተናል ” ያሉት እረፍት የለሹ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ” ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር እየተፋለምንም ቢሆን፣ 5 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል ዕቅዳችንን እናሳካዋለን። እያንዳንዱ ቤተሰብ አካላዊ ርቀትን እንደጠበቀ አሻራውን ማሳረፍ የሚችልበትን መንገድ እናመቻች ” ሲሉም  ኢትዮጵያውያን ለአረንጓዴ አሻራ እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።

LEAVE A REPLY