ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ ሁለት ሜትር የሚረዝሙ ቁጥቋጦዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በአሁኑ ወቅት 15 በመቶ መድረሱን ገለፁ።
የእርሻ መሬት መስፋፋት ለሃገሪቷ የደን ሽፋን መራቆት ጉልህ ሚና ከመጫወቱ ባሻገር፤ የተራቆተውን ያህል የሚተካ ባይሆንም ባለፉት ዓመታት ችግኞች መተከላቸውን የጠቆሙት ሓላፊው፤ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ጥሩ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች መካሄዳቸውን አስታውቀዋል።
በየዓመቱ 5 ቢሊዮን ችግኝ በመትከል አሁን ላይ ያለውን 15 በመቶ የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በሚቀጥለው 10 ዓመት 30 በመቶ እናደርሳለን ሲሉም ኮሚሽነሩ ከወዲሁ አመላክተዋል።