ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች ራሳቸውን በቤት ውስጥ እንዲለዮ መወሰኗ ዋጋ ያስከፍላታል ተባለ

ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች ራሳቸውን በቤት ውስጥ እንዲለዮ መወሰኗ ዋጋ ያስከፍላታል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በሀገሪቱ እየጨመረ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ተጠርጣሪዎች ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዮ መወሰኑ ዋጋ ሊያስከፍለው እንደሚችል ከወዱሁ እየተነገረ ነው።

በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ በለይቶ ማቆያ እንዲሰነብቱ ማድረግ የማይቻል በመሆኑ፤ ራሳቸውን አግልለው ባሉበት እንዲቆዩ ማድረግ ወይም መንግሥት የያዘው አማራጭ ስልት ጉዳቱ የከፋ እንደሚሆን  በተለያዮ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተገለፀ ነው።
ሰሞኑን በግልጽ እንደታየው ናሙና ተወስዶላቸው፣ ውጤት ሳይታወቅ ወደ ሕብረተሰቡ የሚቀላቀሉ ሰዎች መኖራቸው ሓላፊነት የጎደለው ተግባር ነው ያለው የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትም ሆነ የጤና ሚኒስቴር መንግሥት ሁሉንም ተጠርጣሪ የምቀበልበት አቅም ስለሌለኝ ሰዎች ራሳቸውን እንዲለዮ ሲወስን እንዴት በጸጋ ተቀበሉ? በማለት የሚጠይቁም በርካታ ናቸው።
ወረርሽኙ እንዲህ በተስፋፋበት ወቅት ፣ የተለያዮ ሰዎች ከለይቶ ማቆያ ወጥተው ወደ ክልሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪል ሜትሮችን አቋርጠው በሚጠፉበት ሂደት ውስጥ እንዲህ ያለ አቋም በመንግሥት መያዙ በቀጣይ መዘዙ ብዙ ሊሆን ይችላል እየተባለ ነው።
ራስን ለይቶ ለማስቀመጥ የተላለፈውን ውሳኔ ለመተግበር ወይም ለመፈጸም የአኗኗር ሁኔታችን እና አቅማችን አይፈቅድልንም የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ብዙኃኑ ማኅበረሰብ ባልነቃበት አካባቢ አዲሱ መንግሥታዊ ስልት ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍል ከወዲሁ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY