ምክር ቤቱ ሕገ መንግሥቱ ትርጓሜ ላይ ለመወሰን ስብሰባ ሊቀመጥ ነው

ምክር ቤቱ ሕገ መንግሥቱ ትርጓሜ ላይ ለመወሰን ስብሰባ ሊቀመጥ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የፌደሬሽን ምክር ቤት ሀገሪቱ ለምትገኝበት ፖለቲካዊ አጣብቂኝ መፍትኄ ለመሻት ሕገ መንግሥቱ ትርጓሜ ያስፈልገዋል ወይስ አያስፈልገውም የሚለውን ለመወሰን በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚሰበሰብ ተነገረ።

ቀደም ሲል የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ባለፈው ሳምንት የሕገ መንግሥት ትርጓሜ ያስፈልጋል ሲል ለፌደሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳብ ማቅረቡ አይዘነጋም።
የፌደሬሽን ምክር ቤት በቀረበለት የውሳኔ ሐሳብ ላይ ለመወሰን በሚቀጥለው ሳምንት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምክር ቤቱ ገልጿል።
በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 83 ፣ የሕገ መንግሥታዊ ክርክር ጉዳይ ሲነሳ በፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ያገኛል ሲል ይደነግጋል።
የፌደሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥታዊ ጉዳይ ላይ ለሚነሳ ጥያቄ፣ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ምርመራ አድርጎ በሚያቀርብለት የውሳኔ ሐሳብ ላይ በ30 ቀናት ውስጥ ውሳኔ እንደሚሰጥ ሕገ መንግሥቱ በግልጽ አስቀምጦታል።

LEAVE A REPLY