ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ባለፋት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ5 ሺኅ 141 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 150 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚንስትር ገለፀ።
በዚህ መሠረት በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1636 ደርሷል እየተባለ ነው።
በትናንትናው ዕለት ምሽት ላይ በተጨማሪ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን የጠቆመው የጤና ሚኒስቴር፤ በሀገራችን አጠቃላይ ሕይወታቸው ያለፈ ቁጥርም 18 ደርሷል ብሏል።
በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 4 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ብዛት 250 አድርሶታል ያለው መግለጫ፤ ዛሬ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 150 ሰዎች ውስጥ 126ቱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መሆኑን ገልጿል።