ኢትዮጵያና ሱዳን በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት አደረጉ

ኢትዮጵያና ሱዳን በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት አደረጉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የሦስትዮሽ ድርድር ማስቀጠል በሚቻልበት አግባብ ውይይት ተደረገ።

የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ የሚመራ ልዑክ፤ ዛሬ ከሱዳን አቻቸው ፕ/ር ያሲር አባስ ሞሐመድ እና ልኡካቸው ጋር የቪዲዮ ውይይት ማድረጋቸው እየተነገረ ነው።
የሦስትዮሽ ድርድሩ እንደገና ስለሚጀምርበት፣ ስለሚከናወንበት የሥነ ሥርዓት ጉዳዮች እና ግድቡን በተመለከተ የሀገራቱ ዋና ዋና ጉዳዮች እና ሐሳቦችን ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮጵያና ሱዳን የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ የሦስትዮሽ ስብሰባው በቶሎ ለማስጀመር ከስምምነት ላይ እንደ ደረሱ ታውቋል።
በሌላ በኩል ከድርድሩ ጋር የተያያዙ ያልተፈቱ ዋና ዋና ጉዳዮችን በተመለከተም ልዑካኑ ሐሳብ መለዋወጣቸውን የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY