በእንግሊዝ መንገደኞችን ለ14 ቀናት ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዮ የሚያስገድድ ሕግ ዛሬ ተጀመረ

በእንግሊዝ መንገደኞችን ለ14 ቀናት ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዮ የሚያስገድድ ሕግ ዛሬ ተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዮናይትድ ኪንግደም በአውሮፕላን፣ በባቡር ወይም በመርከብ ወደ ዮኬ ሲገቡ መንገደኞች ለ14 ቀናት እራሳቸውን ለይተው እንዲያቆዩ የሚያስገድደው ሕግ ዛሬ ጀምሯል።

በአዲሱ መመሪያ መሠረት የአገሪቱን ዜጎች ጨምሮ ማንኛውም ሰው እራሱን ለይቶ የሚያቆይበት አድራሻ መስጠት የሚኖርበት ሲሆን፤ ይህን ተላልፈው የሚገኙ እስከ 1ሺኅ ፓውንድ ድረስ መቀጮ ይቀጫሉ ተብሏል።
መንግሥት ይህን መተግበር ያስፈለገው ሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት እንዳይከሰት በማሰብ መሆኑም ተነግሯል።
ከሪፐብሊክ ኦፍ አይርላንድ የሚመጡ ዜጎ፣ እንዲሁም የጤና ባለሙያ ሆነው መሠረታዊ አገልግሎት ለመስጠት ወደ ዩኬ የሚገቡ እራሳቸውን ለይተው እንዲቆዮ አይደረገም።
መንገደኞች እራሳቸውን ለይተው የሚያቆዩበት ስፍራ ከሌላቸው፣ በራሳቸው ወጪ መንግሥት ወደ አዘጋጀው ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ እንደሚደረግም ተገልጿል።
ይህ የመንግሥት ውሳኔ ጎብኚዎች ወደ ዩኬ እንዳይመጡ ያደርጋል ሲሉ አንገፎቹ አየር መንገዶች ብርቲሽ ኤር ዌይስ፣ ራይን ኤየር፣ ኢዚጄትን መሰል ተቋማት ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

LEAVE A REPLY