በኮሮና ከተያዙት የጤና ባለሙያዎች መሀል 86 በመቶው ምንም ምልክት አላሳዮም ነበር

በኮሮና ከተያዙት የጤና ባለሙያዎች መሀል 86 በመቶው ምንም ምልክት አላሳዮም ነበር

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያ ውስጥ  በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ አሳሳቢ ሆኗል ተባለ።

ቫይረሱ የተገኘባቸው የጤና ተቋም ሠራተኞች ቁጥር 97 ደርሷል ያለው የጤና ሚኒስቴር መግለጫ፤ አብዛኛዎቹ  በባለፉት ሁለት ሳምንታት የተያዙ መሆናቸውን አስታውቋል።
በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት 97 የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጭዎች መካከል 55 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እንደሆኑ እና ዘጠና አንዱ በአዲስ አበባ የተለያዩ የጤና ተቋማት ላይ የተያዙ እንደሆኑም ታውቋል።
አሁን ላይ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የታወቀው የጤና ባለሙያዎች፤ 86 በመቶ የኮሮና ቫይረስ ምልክት ያልታየባቸው ሲሆን፣ ከመርህ ጋር ተያይዞ በተደረገላቸው ምርመራም የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸውና ቀሪዎቹ ደግሞ መካከለኛ ምልክት እንዳሳዮ  መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በሠላሣ ቀናት ውስጥ በጤና ማዕከላት ከኮቪድ-19 እና ከሌላ ሕክምና ጋር በተያያዘ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የጤና ባለሙያዎቹ ተጋላጭነት እንዲጨምር አድርጎል እየተባለ ነው።
ከሕሙማን ጋር ንክኪ ነበራቸው የተባሉ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር 2340 የደረሰ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል 1 ሺኅ 721 የሚሆኑት ለቫይረሱ የተጋለጡት በመጋቢት ወር እንደሆነና፤ ለቫይረሱ የተጋለጡት የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውን አግልለው የነበሩ፣  በተለያዩ ማዕከላት ውስጥ አገልግልት ላይ የነበሩ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY