የጃዋር መሐመድና የከማል ገልቹ ግጭት ተባብሷል

የጃዋር መሐመድና የከማል ገልቹ ግጭት ተባብሷል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኮ/ል ከማል ገልቹና ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ሌሎች የኦሮሞ ፖለቲከኞችም  መጋጨታቸው እየተነገረ ነው።

ኮ/ል ከማል ገልቹ ከአምስት ወር በፊት የተጣመሩት ኦነግ፣ ኦፌኮ፣ ኦብፓ (እርሳቸው ያቋቋሙት)  ሦሰቱን ድርጅቶች  ለማቀራረብ ጃዋር መሀመድ ምንም ዓይነት ሚና አልነበረውም ማለታቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።
” ጃዋር ወደ እዚህ ሐሳብ የመጣው በስተመጨረሻ ነው:: የሐሳቡ ባለቤትም አልነበረም፤ ይጫወት የነበረው ሚና ሚዲያም፣ ተሰሚነትም ስለነበረው ከኛ የተሻለ ሊሆን ስለሚችል ብለን ነው ያደረግነው እንጂ እርሱ በጥምረቱ ውስጥ ከዛ የዘለለ ምንም ነገር የለውም ” ያሉት ኮለኔል ከማል ገልቹ ሰው ያለ ሥራው ይሸለም፣ ይኮነን ነበር፤ አሁን ግን ሕዝቡ ሀቁን የተረዳ ይመስለኛል፣ ማን ምን ሚና እንደነበረውም ተገንዝቧል ሲሉ ተደምጠዋል።
ጃዋር  እርሱን በግሉ ጣሪያ ሊያደርሰው የሚችለውን መነፅር ትቶ፣ ኦሮሞን እንደ ሕዝብ፣ ከዛም አልፎ ሌላውንም በሚጠቅም መንገድ ቢያስብበት ይሻላል በማለት ከእርሱ ጋር ያላቸውን የፖለቲካ ልዮነት ያመላከቱት የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል የፀጥታና የደህንነት ሓላፊ፤ ጃዋር በዚህ አቅጣጫ አለመሄዱ ብዙ ነገር እያሳጣው ይገኛል።
ጽንፈኝነትን በማራመድ የሚከሰሰው ኦ ኤም ኤን ቴሌቪዥን ነፃነት ላይ ትልቅ ጥያቄ እንዳላቸውና፤ ሚዲያው ከጃዋር ሓሳብ መላቀቅ ካልቻለ  ቁልቁል እንደሚሄድ አልጠራጠርም   ሲሉም ተደምጠዋል።
“ለነፃነት እየታገልን፣ ሐሳብ ነፃነት እየታገልን የሚመቸንን እና እንዲሰማ የምንፈልግውን ድምፅ ብቻ እንዲሰማ የምናደርግ ከሆነ ለምድነው መንግሥትን የምንቃወመው፣ የምንታገለው?  ስለአንድ ሰው ገናናነት ወይም ጃዋር ሰለገባበት ቡድን ድምፅ ብቻ ሰማይ የምታደርስ ከሆነ ከብልፅግና ፓርቲ በምን ትሻላለህ?” ያሉት የጦር መኮንን ከጃዋር ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን በግልጽ አሳይተዋል።
አሁን ላይ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዮት ከሆነ በጥምረት ውስጥ የቆዮት ሥስቱ ፓርቲዎች እየተፍረከረኩና ልዮነታቸው እየሰፋ መሆኑን ያሳያሉ። በፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች በቀለ ገርባ፣ ከማል ገልቹ ፣ ዳውድ ኢብሳና ጃዋር መሐመድን ጨምሮ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ አባሎቻቸው ጭምር እርስ በርስ መከፋፈልና መቆራቆዝ ጀምረዋል።

LEAVE A REPLY