136 ሰዎች ዛሬ ኮሮና ተገኘባቸው፣ 32 ሰዎች ጽኑ ሕሙማን ክፍል ገብተዋል

136 ሰዎች ዛሬ ኮሮና ተገኘባቸው፣ 32 ሰዎች ጽኑ ሕሙማን ክፍል ገብተዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ በተደረገ ለ4ሺኅ 775 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሠላሣ ሥድሥት (136) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በዚህ መሠረት በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2156 ሊደርስ ችሏል።
ዛሬ የኮቪድ 19 ቫይረስ እንደተገኘ የተረጋገጠባቸው ሰዎች ከ1 እስከ 97 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ  85 ወንድና 51 ሴቶች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የገለፀው የጤና ሚኒስትር፤ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 115ቱ ከአዲስ አበባ፣ 7 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 9 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ሰዎች ከሐረሪ እና 2 ሰዎች ከሶማሌ ክልል እንዲሁም አንድ ሰው ከደቡብ ክልል መሆናቸውን ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ሕክምና ውስጥ 1 ሺኅ 766 ሰዎች ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ። ከነዚህም ሠላሣ ሁለት ሰዎች በጽኑ ሕክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የጤና ሚኒስትር መግለጫ ያሳያል።
ትናንት ዐሥራ ሠባት (17) ሰዎች (8 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከአማራ ክልል፣ 2 ከአፋር ክልል እና 2 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል) ማገገማቸውን ተከትሎ ፣  በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 361 መድረሱም ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY