በኩዌት የሚገኙ 230 ኢትዮጵያውያን  በመጀመሪያው ዙር ዛሬ ወደ ሀገራቸው ይገባሉ

በኩዌት የሚገኙ 230 ኢትዮጵያውያን  በመጀመሪያው ዙር ዛሬ ወደ ሀገራቸው ይገባሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኮሮና ቫይረስን ተከትሎ በተለያዮ አረብ ሀገራት የሚገኙ ዜጎች ያቀረቡትን የድረሱልን ጥሪ ተከትሎ ስደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ላይ የሚገኘው ፊቱን ወደ ኩዌት አዙሯል።

በነዳጅ ምርቷ በምትታወቀው ኩዌት ወረርሽኙን ተከትሎ  ሥራ የፈቱና በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በቅድሚያ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ መሰናዶውን ማጠናቀቁ ተሰምቷል።
እነዚህ በኩዌት በጊዜያዊ መጠለያዎችና በዲፖርቴሽን ማዕከል የነበሩ 250 ዜጎች ዛሬ ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ።
በመጀመሪያ ዙር ኢትዮጵያ የሚገቡት ከስደት ተመላሾችን በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር  አብዱልፈታህ አብዱላሂ፣ የኤምባሲው ዲፕሎማቶችና ሠራተኞች በኩዌት ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ሽኝት እንዳደረጉላቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY