190 ሰዎች ዛሬ በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፤  5 ሰዎችም  ሕይወታቸው አልፏል

190 ሰዎች ዛሬ በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፤  5 ሰዎችም  ሕይወታቸው አልፏል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ  ለ4 ሺኅ 599 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 190 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለፀ።

ይህንን ተከትሎ በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺኅ 336 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አረጋግጧል።
ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ፤ 135 ወንድና 55 ሴት፣ የዕድሜ ክልላቸውም ከ1 እስክ 89 ዓመት የሚደርስ መሆኑ ተነግሯል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 153 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ 16 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ሰዎች ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል፣ 10 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 3 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ እንዲሁም 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል እንደሆኑም መግለጫው ያሳያል።
በተያያዘ ዜና ዛሬ 5 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ ሕይወታቸው ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
ከሟቾች መካከል 2ቱ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ፣ 3ቱ ደግሞ በሕክምና ማዕከል በሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል።
በሀያ አራት ሰዐት ውስጥ የተመዘገበውን አምስት ሞት ተከትሎ  አጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 32 ደርሷል።
በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ብቻ18 ሰዎች (11ዱ ከአዲስ አበባ፣ 5ቱ ከአማራ ክልል፣ 2ቱ ሱማሌ ክልል) ያገገሙ በመሆናቸው፤  እስካሁን በሀገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 379 መድረሱን ያስታወቀው የሚኒስቴሩ መግለጫ፤ በአሁኑ ወቅት 1ሺኅ 923 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸው ሕክምና እየተከታተሉ እንደሆነና 32 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ እንደሚገኙ ሕዝብ ይወቅልኝ ብሏል።

LEAVE A REPLY