በምዕራብ ወለጋ የኮሮና ቫይረስ ውጤት በመሳሳቱ 300 ግለሰቦችና ሐኪሞች ኳራንቲ ገቡ

በምዕራብ ወለጋ የኮሮና ቫይረስ ውጤት በመሳሳቱ 300 ግለሰቦችና ሐኪሞች ኳራንቲ ገቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ መንዲ ከተማ ነዋሪ የሆነ ወጣት በስህተት ቫይረሱ የለብህም ከተባለ ከቀናት በኋላ “የተነገረህ ውጤት የሌላ ሰው ነው ” በሚል እርሱን ጨምሮ ከእርሱ ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ በርካታ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸው ተሰማ።

ግለሰቡ ሕመም ተሰምቶት ወደ የግል የጤና ማዕክል ሁለት ጊዜ ሄዶ እንደነበረ የገለፁት የመንዲ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ገመቹ ጉዲና  “እኛ ሆስፒታል እንደደረሰ ወደ ለይቶ ማቆያ አስገብተን፤ ናሙናው ለምርመራ ተላከ። ከዚያ ቅዳሜ ዕለት ቫይረሱ እንደሌለበት ተነገረን። ሰኞ ደግሞ የደረሳችሁ ውጤት የሌላ ሰው ነው አሉን። የመጀመሪያው ውጤት ስህተት እንደሆነና ግለሰቡ በሽታው እንዳለበት ነገሩን። ከዚያም መልሰን ወደ ለይቶ ማቆያ አስገባነው” በማለት የአሠራር ክፍተቱን አጋልጠዋል።
ወጣቱ በቅርቡ በአንድ በርካታ ሰው በተሰበሰበበት ማኅበራዊ ሥነ ሥርዓት ላይ መታደሙንና ከበርካታ ሰዎች ጋር ንክኪ እንደነበረው የገለፁት ዶክተር ገመቹ፤ ይህን ተከትሎ  ቤተሰቦቹንና 15 የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ከወጣቱ ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ 300 ሰዎች ለይቶ ማቆያ ገብተዋል።

LEAVE A REPLY