ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ከትናንት በስቲያ በገዛ ፍቃዴ ሥልጣኔን ለቅቂያለሁ ባሉት ወ/ሮ ኬሪያ ምትክ የቀድሞ የሶማሌ ክልል ም/ርዕስ መስተዳድር አቶ አደም ፋራህን የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አድርጎ ሾሟል፡፡
በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ በትክክል እየተገበሩ ነው የሚባሉት የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የሙስጠፌ ቅኝ እጅ የሆኑት አዲሱ ተሿሚ አደም ፋራህ፤ የሱማሌ ክልልን በምክትል ትሬዝዳንትነት ሲመሩ እንደነበር የሥራ ልምዳቸው ያሳያል።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ ወ/ሮ እፀገነት መንግሥቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል፡፡