ሁለቱ ምክር ቤቶች የሕዝብ ቆጠራ  ለሦስተኛ ጊዜ እንዲራዘም አፀደቁ

ሁለቱ ምክር ቤቶች የሕዝብ ቆጠራ  ለሦስተኛ ጊዜ እንዲራዘም አፀደቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ለአራተኛ ጊዜ ይካሄዳል ተብሎ የተጠበቀው የኢትዮጵያ ሕዝብና ቤት ቆጠራ ለሦስተኛ ጊዜ እንዲራዘም ሁለቱም ምክር ቤቶች ወሰኑ።

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባካሄዱት ስብሰባ፤ 4ኛውን የሕዝብና ቤት ቆጠራ ለሦስተኛ ጊዜ ለማራዘም የተዘጋጀውን የውሳኔ ሐሳብ ተመልክተው ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።
ሁለት ጊዜ የተራዘመው የሕዝብና ቤት ቆጠራ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት፣ ለሕዝብ ጤናና ደህንነት ሲባል ለሦስተኛ ማራዘም አስፈላጊ ነው በሚል የቀረበው ሐሳብ ላይ የምክር ቤቶቹ አባላት ውይይት ካደረጉ በኋላ፤ ቆጠራው እንዲራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ በ5 ተቃውሞ፣ በ13 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ ማፅደቃቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY