ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከቀናት በፊት በሸኘነው ወርሃ ግንቦት 23.6 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ፣ 18.35 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 77.8 በመቶ ማሳካቱን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ።
ከሀገር ውስጥ ታክስ 10.4 ቢሊየን ብር የተሰበሰበ፤ ከውጪ ቀረጥና ታክስ 7.9 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የጠቆመው ሚኒስቴሩ፤ ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ3.8 ቢሊየን ብር ወይም የ20.15 በመቶ ዕድገት እንዳሳየ አስታውቋል።
በ2012 በጀት ዓመት በ11 ወራት ውስጥ 242.94 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ፣ 217.24 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ ከባለፈው በጀት ዓመትም 21.74 በመቶ ዕድገት ሊታይ ታይቷል።
ተቋሙ የ2012 በጀት ዓመት 270 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ እቅድ ተይዞ፤ 217.24 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ ተቋሙ እቅዱን 89 ፐርሰንት ለማሳካት ችሏል።
በተያያዘ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ዐቀፍ የተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ሚኒስቴሩ ግብር ከፋዮችም በወሩ መጨረሻ ያለውን መጨናነቅ ሳይጠብቁ የኢ-ታክስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚጠበቅባቸውን ግብር መክፈል እንዲቀጥሉ መልዕክት አስተላልፏል።