ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ስለ ምጣኔ ሀብት ማገገምና ስለ አዲስ የዕድገት አቅጣጫ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል ተባለ።
“ታላቁ ዳግም ማስጀመሪያ” የሚል መርህ ቃል ባነገበው ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ያደረጉት በኦን ላይን ስብሰባ መሆኑም ተሰምቷል፡፡
የወረርሽኙን ዓለም ዐቀፋዊ ውስብስብነት እና ለመላመድ ያለውን ፈተና ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ችግሩ ሊፈታ የሚችለው በጋራ በሚወሰዱ እርምጃዎች እና በዓለም ዐቀፍ ትብብር ብቻ መሆኑንም ተናግረዋል።
“የአሁኑ ዓለም ዐቀፋዊ ገጽታ በታሪክ ውስጥ አዲስ አስተሳሰብ ፈጥሮአል፤ የጋራ ፍላጎትን በመወከል የአዋቂ አስተሳሰብን እና ድፍረትን ሊጠቀም የሚችል የዓለም ዐቀፍ አመራር ክፍተት አለ” የሚል መልእክት በጉባዔው ላይ ማስተላለፋቸው ተሰምቷል።