ማስተንፈሻ ያላቸው ማስኮች የጥራት ማረጋገጫ ያልተሰጣቸው ናቸው ተባለ

ማስተንፈሻ ያላቸው ማስኮች የጥራት ማረጋገጫ ያልተሰጣቸው ናቸው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ማስተንፈሻ ያላቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስኮች ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋት ሚናቸው የጎላ ነው አለ።

ማስተንፈሻ  ያላቸው ማስኮች የተዘጋጁት ለኢንዱስትሪ ዓላማ ታስቦ በመሆኑ፣ አየር ወደ ውጪ በማስወጣታቸው ምክንያት ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው ትንፋሽ በቀላሉ እንዲተላለፍ ያደርጋሉ ሲልም የስጋቱን ምንጭ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።
ብዙዎች የሚጠቀሙት ማስተንፈሻ ያለውን ማስክ ያደረገ ግለሰብ ወደ ውስጥ ምንም አየር የማያስገባ በመሆኑ በቫይረሱ የመያዝ እድሉ በእጅጉ የጠበበ ቢሆንም፤ ነገር ግን ማስኩ ወደ ውጪ አየር የሚያስወጣ በመሆኑ ፣ ራስ ወዳድ የሆነ የፊትና የአፍንጫ ጭምብል ነው ተብሎለታል።
የኮሮና ወረርሽኝ የመከላከያ መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ጊዜያዊ ፈቃድ በማውጣት 300 የሚሆኑ ድርጅቶች ወደ ተግባር የገቡ ቢሆንም፣ በአሁን ሰዐት በተግባር ሥራቸውን እየሠሩ የሚገኙት  147 ድርጅቶች ናቸው።
 በገበያ ላይ በስፋት የሚስተዋሉት ባለ ማስተንፈሻ የፊት ጭምብሎች በባለስልጣን  መሥሪያ ቤቱ የጥራት ማረጋገጫ ያላገኙ ናቸው ተብሏል።

LEAVE A REPLY