ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ የሦስትዮሹ ጉባዔ እንደቀጠለ የኢትዮጵያ የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ሊቀመንበርነት እየተካሄደ ባለው ድርድር፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያው የውሃ አሞላል እና አጠቃላይ ዓመታዊ አለቃቀቅ ላይ መምከሩ ተሰምቷ
ሱዳን ባቀረበችው የድርድር እና የመወያያ ምክረ ሐሳብ ላይም ሀገሮቹ ሐሳባቸውን በማቅረብ የተወያዮበት ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የሦስቱ ሀገሮች ስምምነት እና ድርድር የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ እንዲሆን እንደምትፈልግ በአፅንኦት መናገሯን የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስነብቧል።
ከትናንት በስቲያ የተጀመረውና በቪዲዮ ክኮንፍረንስ የታገዘው ጉባዔ ላይ የቴክኒካል ድርድሩ በሦስቱም ሀገሮች ጥቅም ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ፍላጎቷ መሆኑን ኢትዮጵያ የገለጸች ሲሆን፣ ነገ ቅዳሜ የሦስትዮሽ ምክክሩ በሱዳን ሊቀመንበርነት ሲቀጥል ደግሞ የተለዮ ሐሳቦች በውይይቱ ሊሰሙ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በታላቁ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ የቪዲዮ ኮንፍረንስ ላይ ደቡብ አፍሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት እና የአሜሪካ መንግስት በታዛቢነት የሚያደርጉትን ተሳቶትፎ ቀጥለዋል።
ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የሚያደርጉት ተከታታይ ውይይት የግድቡን የመጀመሪያ ውሃ ሙሌት እና ዓመታዊ አለቃቀቅ ላይ ብቻ ማተኮሩም ታውቋል።