የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዓመቱ ሳያልቅ ምርጫ እንዲካሄድ ወስኛለሁ አለ

የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዓመቱ ሳያልቅ ምርጫ እንዲካሄድ ወስኛለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የትግራይ ክልል ምክር ቤት ይህ ዓመት ከማለቁ በፊት በክልሉ ምርጫ እንዲደረግ መወሰኑ ተገለፀ።

መቶ በመቶ በህወሓት ነባር ታጋዮችና የድርጅቱ ታማኝ አባላት የተሞላው የትግራይ ክልል ምክር ቤት፤ ክልላዊ ምርጫው ይህ ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት እንዲካሄድ ወስኗል።

ተወሰነ የተባለውን ሐሳብ አስመልክቶ ለቢቢሲ ገለጻ ያደረጉት የትግራይ ክልል ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ታረቀ  ምርጫው ከጵጉሜ በፊት እንዲካሄድ መወሰኑን በምክር ቤቱ መወሰኑን አስታውሰው ህወሓት በታቀደው ጊዜ ምርጫውን ለማካሄድ ዝግጁ ነው ብለዋል።
ዘንድሮ ነሐሴ መጨረሻ ላይ ለማካሄድ ታቅዶ የነበረውን አገራዊ ምርጫ በኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ምክንያት ማከናወን አልችልም ሲል ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል መግለፁ ይታወሳል።
ዛሬ ስብሰባ የተቀመጠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ቀጣዮን ክልላዊ ምርጫ የያዝነው ዓመት ሳይጠናቀቅ አካሂዳለሁ በማለት ቢወስንም፣ ይህ ሐሳብ በምርጫ በረደና በስብሳቢዋ ወይዘሪት ብርቱኳን ሚዴቅሳ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ አይጠበቅም።

LEAVE A REPLY