የአስከሬን ምርመራ ውጤት አንድ ሳምንት መፍጀቱ ሀዘንተኞችን ክፉኛ እየጎዳ ነው ተባለ

የአስከሬን ምርመራ ውጤት አንድ ሳምንት መፍጀቱ ሀዘንተኞችን ክፉኛ እየጎዳ ነው ተባለ

A coronavirus diagnostic test kit sits displayed in this arranged photo at the TIB Molbiol Syntheselabor GmbH production facility in Berlin, Germany, on Thursday, March 6, 2020. TIB has reoriented its business toward coronavirus, running its machines through the night and on weekends to make the kits, which sell for about ???160 ($180) apiece. Photographer: Krisztian Bocsi/Bloomberg

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ የሚሞቱ ሰዎች በጠቅላላ የአስከሬን ምርመራ እንዲደረግላቸው የሚያስገድደው አሠራር ከፍተኛ የሆነ መጓተት እንዳለበት ተነገረ።

በተለይም ባለፉት ሁለት ሳምንታት በርካታ ሰዎች ከሞቱ በኋላ በተደረገላቸው ምርመራ (አንዳንዶቹ ደም ሰጥተው ውጤት ሳይደርስ ሕይወታቸው ያለፈ ነው) የኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው በላብራቶሪ መረጋገጡ አሠራሩ በዋና መመሪያነት እንዲቀመጥ አድርጎታል።
የአስከሬን ምርመራ መደረጉ ለሁሉም ህብረተሰብ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ባይካድም አንድ ሰው ሞቶ አስከሬኑ ለምርመራ ማረጋገጫ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ በምንም ይሙት በምን ውጤት ለማግኘት ከአራት ቀን እስከ አንድ ሳምንት መጠበቅ መደበኛ አሠራር እየሆነ መጥቷል ብለዋል አስተያየት ሰጪዎቹ።
ይህንን የሕዝብ እሮሮና ያለውን መጓተት በደንብ ተገንዝቢያለሁ ያለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በበኩሉ፤ ምርመራው እንዲፈጥን ሌሎች ዘዴዎችም ካሉ እነርሱን ለመጠቀም ከሙያተኞችና ጉዳዮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየመከርኩ ስለሆነ ኅብረተሰቡ ትንሽ ሊታገሰኝ ይገባል ብሏል።

LEAVE A REPLY