በኢትዮጲያ የሟቾች ቁጥር 55 ደረሰ፣ ዛሬም 268 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል

በኢትዮጲያ የሟቾች ቁጥር 55 ደረሰ፣ ዛሬም 268 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ  ለ5 ሺኅ 544 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 268 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፡፡ ይህን ተከትሎ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር  3 ሺኅ166 ደርሷል።

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 177 ወንድ እና 91 ሴት ሲሆኑ፣ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 90 ዓመት ውስጥ እንደሆነና ከአንድ ሰው በስተቀር ሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል በዛሬው ዕለትም ስምንት ሰዎች በኮቪድ 19 ቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 55 ደርሷል።
ሚኒስቴር መ/ቤቱ ባወጣው መግለጫ መሰረት ዛሬ መሞታቸው ይፋ የተደረጉት፤
1ኛ- የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ወንድ 65 ዓመት በህክምና ላይ የነበሩ፣
2ኛ – የአዲስ አበባ ነዋሪ ሴት 34 ዓመት በህክምና ላይ የነበረች፣
3ኛ – የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ወንድ 45 አመተ በህክምና ላይ የነበረ፣
4ኛ – የአዲስ አበባ ነዋሪ ሴት 40 ዓመት በህክምና ላይ የነበረች፣
5ኛ- የአዲስ አበባ ነዋሪ ወንድ 90 ዓመት  በአስክሬን ምርምራ ቫይረሱ የተገኘ፣
6ኛ – የአዲስ አበባ ነዋሪ ወንድ – በአስክሬን ምርምራ ቫይረሱ የተገኘ፣
7ኛ – የአዲስ አበባ ነዋሪ ወንድ 50 እድሜ  በአስክሬን ምርምራ ቫይረሱ የተገኘ፣ 8ኛ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሴት 45 እድሜ በአስክሬን ምርምራ ቫይረሱ የተገኘበት መሆናቸው ታውቋል።
 ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 268 ሰዎች ውስጥ  232 ሰዎች የአዲስ አበባ፣ 12 ሰዎች የኦሮሚያ ክልል፣ 6 ሰዎች የትግራይ ክልል፣ 2 ሰዎች የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ፣ 2 ሰዎች የአፋር ክልል፣ 8 ሰዎች የአማራ ክልል፣ 5 የሀረሪ ክልል እና 1 የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ነዋሪዎች መሆናቸው ተነግሯል።

LEAVE A REPLY