ግብፅ ድርድሩ እየተደረገ የውሃ ሙሌት መካሄድ የለበትም ስትል ተቃውሞዋን አሰማች

ግብፅ ድርድሩ እየተደረገ የውሃ ሙሌት መካሄድ የለበትም ስትል ተቃውሞዋን አሰማች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መካከል በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው ድርድር ትናንት በቀጠለበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ በድርድሩ ሁለት የቴክኒክና የህግ ቡድኖች ቢኖሩ በሚል ያቀረበችውን ሐሳብ ሱዳን መቀበሏን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

የህዳሴው ግድብ ግንባታ ፈጽሞ ያልተዋጠላት ግብፅ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ሳትቀበለው የቀረችውን፣ ረዘም ያለ የድርቅ ጊዜን እና ደረቃማ ዓመትን በተመለከተ ዝርዝር ህግ ሊኖር ግድ ነው የሚለውን ግትር ሐሳቧን ዳግም ይዛ ቀርባለች ነው የተባለው።
በዕለቱ በነበሩ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ በተካሄደ ድርድር ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ አሞላል በተመለከተ ባቀረበችው ሐሳብ ላይ ውይይት ተካሂዷል ያለው ሚኒስቴሩ፤
ይህን ተከትሎ የመጀመሪያው ዙር የግድቡን የውሃ አሞላል እና አሞላሉ የሚገዛበት መመሪያን በተመለከተ ኢትዮጵያ ባቀረበችው ሃሳብ ለመቀጠል ከመግባባት ተደርሷል ሲል አስታውቋል።
በግብፅ በኩል የተነሳውንጰረዥም ድርቅን በተመለከተ የቴክኒክ ኮሚቴ የውሃ አለቃቁ ላይ ህግን እንዲያዘጋጅ ሓላፊነት እንዲሰጠው ፣  ዝርዝር አለቃቀቅን በተመለከተ ግን ድርድር ማድረግ አስፈላጊ ነው ከሚል መግባባት ላይ ሀገራቱ እንደደረሱ ተሰምቷል።
የግድቡን ደህንነት የተመለከተ ህግ እና ግድቡ በሚኖረው አካባቢያዊ እና ማኅበራዊ ተፅእኖ ጥናት ማስፈለግ ላይ ሦስቱ ሀገራት ከመግባባት ላይ እንደደ ደረሱ የሚያመላክተው መግለጫ፤ የግብፅ ተደራዳሪዎች በእለቱ የነበራቸው ተሳትፎ የተቀዛቀዘ  እንደ ነበር ያሳያል።
የግብፅ ተደራዳሪዎች ውይይት ሲደረግበት በነበረው እና  ቀደም ሲል በእነርሱ በኩል  ሊያሠራ የሚችል ሰነድ ነው ብለው አስተያየት የሰጡበትንና ሱዳን ያቀረበችውን ሰነድ በውይይቱ መጨረሻ ላይ መልሰው ተቃውመውታል።
በሐሳቡ ላይ ሀገራቸው ያላትን አቋም ይዘው እንዲቀርቡ መጠየቃቸውን የተቃወሙት ግብፃውያኑ፣ ድርድሩ እየተካሄደ የግድቡ ውሃ ሙሌት ሊካሄድ አይገባም ሲሉ ከመቃወማቸው ባሻገር፤  እየተካሄደ ያለው ድርድር ሰኞ እንዲጠናቀቅ ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በግድቡ ዙሪያ  እስካሁን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ያስቀመጧቸው፣ በድርድሩ ለተገኙ ለውጦች እውቅና ላለመስጠት ግብፅ ፍላጎት ማሳየቷን የሚያስረዳው የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፤ ድርድሩ ዛሬ (እሁድ) ሲቀጥል የተደረጉ ድርድሮችን መሰረት በማድረግ በተዘጋጁ መመሪያዎች እና ህጎች ላይ ሐሳብ ይለዋወጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ግምቱን አስቀምጧል።

LEAVE A REPLY