በደብረ ብርሃን ከተማ መናኸሪያ ከሚሠሩ 36 ሠራተኞች 16ቱ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

በደብረ ብርሃን ከተማ መናኸሪያ ከሚሠሩ 36 ሠራተኞች 16ቱ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ወረርሽኙ እየተስፋፋባት እንደሆነ በሚነገርላት በደብረ ብርሃን ከተማ  በአንድ መ/ቤት ውስጥ ከሚሠሩ ሠራተኞች መሀል ግማሽ ያህሉ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነገረ።

በከተማ  አስተዳደር መናኸሪያ ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጡ 36 ግለሰቦች ቫይረስ ምርመራ ናሙና ተወስዶ በ16ቱ ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጠቆመው መረጃ፤ ግለሰቦቹ በመናኸሪያው በተለያየ የሥራ ዘርፍ የተሠማሩ ሠራተኞ፣ሹፌሮችና ረዳቶች መሆናቸውን አስታውቋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት  ሓላፊ አቶ ጌታሁን ማሞ  ቅዳሜ ዕለት በ06/10/2012 ዓ.ም  የጽሕፈት ቤቱ የጤና ባለሙያዎች ከ36 የደብረ ብርሃን መናኸሪያ ሠራተኞች፣ሹፌሮችና እረዳቶች ላይ ናሙና ተወስዶ ፣ ናሙና ከሰጡት 36 ሰዎች ውስጥ 16ቱ  የ(covid-19) ቫይረስ ስለ ተገኘባቸው፤ ጠባሴ ጤና ጣቢያ የሕክምና ማዕከል እንዲገቡ መደረጋቸውን ገልፀዋል።
ከግለሰቦቹ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች እየተለዩ መሆናቸውን፣ በተመሳሳይ ዛሬም በዚያው በደብረ ብርሃን ከተማ መናኸሪያ አካባቢ የ70 ሰዎች ናሙና ተወስዶ ውጤት እንደሆነ ሓላፊው አስረድተዋል።
ማኅበረሰቡ  ከቫይረሱ እንዲጠነቀቅ በተደጋጋሚ ቢነግርም፣ የባህሪ ለውጥ ባለማምጣቱ በከተማው ከመቸውም ጊዜ በበለጠ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተስፋፋ እንደሆነ የደብረብርሃን ከተማ የጤና ቢሮ ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY