ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በግብጽ በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ሕይወታቸው ያለፈ ዶክተሮች ቁጥር 60 ደርሷል ተባለ፡፡
የግብፅ የሕክምና ባለሞያዎች መንግሥት በቂ የሕክምና ቁሳቁስ እንዲያሟላ በተደጋጋሚ እየጠየቁ ሲሆን፣ ትናንትም በተመሳሳይ ሁኔታ በካይሮ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ የሚሠሩ የልብ ቀዶ ሕክምና ዶክተርም በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ለሕክምና ባለሞያዎች በቂ መከላከያ መንግሥት እያቀረበ ባለመሆኑና በዚህ ግድ የለሽነት ከ60 በላይ ሀኪሞች በቫይረሱ መሞታቸውን ይፋ ያደረገው የግብፅ የሐኪሞች ማኅበር፤ እስካሁን በግብፅ 44 ሺኅ 598 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች እንዳሉ፣ ከእነርሱ መሀልም 1 ሺኅ 575 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን አስታውቋል።
በአፍሪካ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር በእጅጉ ማሻቀቡን ተከትሎ፤ 242 ሺኅ 105 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፣ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 6 ሺኅ 464 መድረሱ ተሰምቷል። በአንጻሩ 125 ሺኅ 664 አፍሪካዊያን ደግሞ ከበሽታው ማገገም ችለዋል።