ኢትዮጵያ ኮሮናን በአግባቡ እንድትከታተል የአውሮፓ ኅብረት 19 ቢሊዮን ብር እረዳለሁ አለ

ኢትዮጵያ ኮሮናን በአግባቡ እንድትከታተል የአውሮፓ ኅብረት 19 ቢሊዮን ብር እረዳለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና የአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያ 19 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ሊያደርግ እንደሆነ ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከፍተኛ መስፋፋት እያሳየ የሚገኘውን የኮቪድ 19 ቫይረስን መቆጣጠር ተገቢ መሆኑን እንደሚያምንበትም ኅብሰቱ አስታውቋል።
በዚህ መሠረት  የአውሮፓ ኅብረት ኢትዮጵያ ላጋጠማት የኮሮና ቫይረስ ቀውስ ምላሽ መስጠት እንድትችል ከላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ድጋፍ አደርጋለሁ ብሏል።
ሀገሪቱ የጤና ሥርዓቷን ለመደገፍ፣ የማቆያ ማዕከላት እንድትገነባ፣ የኑሮ እና ኢኮኖሚ መነሣሣት እንድትፈጥር የሚያስችል የ487 ሚሊየን ዩሮ ወይንም 19 ቢሊዮን ብር  ድጋፍ እሰጣለሁ ያለው ኅብረቱ፤  ድጋፉን ማድረግ ያስፈለገው፣ አጋር አገራት ወረርሽኙን ለመቋቋም እንዲችሉ መሆኑም ተገልጿል።

LEAVE A REPLY