የሚኒስትሮች ም/ቤት በተለያዩ ህጎችን አፀደቀ

የሚኒስትሮች ም/ቤት በተለያዩ ህጎችን አፀደቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 85ኛ መደበኛ ስብሰባ በንግድ ህግና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬ ውሎው በኢትዮጵያና በኮርቤቲ የኃይል ግዢ ስምምነት፣ በረቂቅ የንግድ ህግ፣ እና ረቂቅ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራተጂ ላይ ተወያይቶ የማጽደቅ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
ከኮርቤቲ ጋር የሚደረገው የኃይል ግዢ ስምምነት የተጠናቀቀው፣ መንግሥት ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት በማካሄድ ረዥም ዓመታትን የጠየቁ ሥራዎችን ካከናወነ በኋላ መሆኑን መረጃው አሳይቷል።
በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ መካከል የሚከወን የጥምረት ሥራ፣ የውጪ አካላት በቀጥታ መዋዕለ ነዋይ ለማፍሰስ የሚችሉበትን የጂኦተርማል እና የኢነርጂ አዋጆችን፣ እንዲሁም የግሉ ዘርፍ በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይ ለማፍሰስ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማካሄድ የሚችልባቸውን ሁኔታዎች በአግባቡ በማጥናት ማጽደቅ የእዚህ ሥራ አካል እንደሆነም ተነግሯል።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ የተወያየበት አንዱ የረቂቅ ንግድ ነው። የረቂቅ ንግድ የፀደቀው ነባሩ የንግድ ሕግ ከፀደቀ፣ ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በኋላ ሲሆን፣ የሕግ ሥርዓቱን ለማዘመን በሚደረገው ሂደት ውስጥ አንድ ምዕራፍ ነው ተብሎለታል።
የፀደቀው አዲሱ የንግድ ህግ የበለጸገ ማኅበረሰብ ለመገንባት ያለንን መሻት ባማከለ መልኩ፣ የፈጠራ እና የንግድ ሥራዎች ክንውንን የሚያነሳሳ መሆኑ በስብሰባው ላይ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መብራት ኃይል ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር በአንድ በኩል፣ የኮርቤቲ እና ቱሉ ሞዬ ኩባንያዎች ደግሞ በሌላ በኩል በመሆን፣ በመንግሥት እና በግል ዘርፍ መካከል የሚካሄደውን ጥምረት በመከወን በአጠቃላይ 300 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል ኃይል እንደሚያመነጭ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ጂኦተርማል ዘርፍ እና ተያያዥ ክሂሎቶች፣ የኢትዮጵያን የኃይል ዐቅም፣ ዋስትናን እንዲሁም አስተማማኝነት በሚያረጋግጥ መልኩ ይህንን አረንጓዴ፣ ንጹሕ እና ታዳሽ የኃይል ምንጭ በጥቅም ላይ እንደሚያውሉ የተነገረ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ መንግሥት፣ የፈጠራ ሥራዎች እና ዲጂታል አገልግሎቶችን በማስፋፋት ሁሉን አካታች ዕድገት ለማምጣት የሚያከናውነው ሥራ ማዕከል እንደሆነም ተብራርቷል።

LEAVE A REPLY