ሜ/ጀነራል ከፍያለው አምዴ የተባበሩት መንግሥታት ጦር አዛዥ እንዲሆኑ በአንቶኒዮ ጉተሬዝ ተሾሙ

ሜ/ጀነራል ከፍያለው አምዴ የተባበሩት መንግሥታት ጦር አዛዥ እንዲሆኑ በአንቶኒዮ ጉተሬዝ ተሾሙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ሜጀር ጀነራል ከፍያለው አምዴ ተሰማ በአብዬ ግዛት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጊዜያዊ የፀጥታ ኃይል ዋና አዛዥ ሆነው ተሾሙ፡፡

ቀደም ሲል በሓላፊነት ጦሩን ይመሩ የነበሩት ሜጀር ጀነራል መሃሪ ዘውዴ ገ/ማርያምን በመተካት ፣ ጀነራል ከፍያለው በግዛቲቱ የፀጥታ ሀይል ዋና አዛዥ አድርገው የሾሟቸው የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ናቸው፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ኃይል የአብዬ ግዛት ዋና አዛዥ ሆነው የተሾሙት ሜጀር ጀነራል ከፍያለው አምዴ ተሰማ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ለ30 ዓመታት ያገለገሉ ናቸው። ሜጀር ጀነራሉ በኢትዮጵያ
ሀገር መከላከያ ሰራዊት ውስጥ የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሆነውም ሠርተዋል።
ጀነራል ከፍያለው በቢዝነስ አስተዳደር 2ኛ ዲግሪ ከአሜሪካው አሽላንድ ዩኒቨርስቲ፣ እንዲሁም በወታደራዊ አንድነትና አሰላለፍ የመጀመሪያ ድግሪ ከሩሲያ የጦር ማሰልጠኛ ያገኙና ዕድሜያቸውም 51 ዓመት እንደሆነ የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

LEAVE A REPLY