ዲክሳሜታሶን የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ መድኃኒት መሆኑ ተረጋገጠ

ዲክሳሜታሶን የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ መድኃኒት መሆኑ ተረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዲክሳሜታሶን የተሰኘው የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ መድኃኒት እንደሆነ የብሪታኒያ ተመራማሪዎች አረጋግጠናል አሉ።

በዓለም ላይ በርካሽ ዋጋ እንደሚገኝ የሚነገርለት ዲክሳሜታሶን የተሰኘው መድኃኒት  በፅኑ ሕክምና ላይ የሚገኙ የኮሮና ቫይረስ ሕሙማንን ለማከም ጥቅም ላይ ቢውል ለማገገም እንደሚያስችል በመነገር  ላይ ነው።
የብሪታኒያ ተመራማሪዎች አነስተኛ መጠን ያለው የዲክሳሜታሶን መድኃኒት ገዳይ ለሆነው የኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ሁነኛ መድኃኒት እንደሆነ ከማረጋጣቸው ባሻገር፤ መድኃኒቱ  በአጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያዎች ለሚተነፍሱ ሕሙማን በሦስት በመቶ ሞትን መቀነስ ሲያስችል ያለ አጋዥ መተንፈሻ ለሚተነፍሱ ደግሞ አምስት በመቶ ሞትን መቀነስ ችሏል ብለዋል።
 መድኃኒቱ በከፍተኛ ደረጃ የሙከራ ሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፤ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ደግሞ ለኮሮና ቫይረስ መድኃኒቱ ያለው ፈዋሽነት በመሞከር ላይ መሆኑ ተገልጿል።
በብሪታኒያ መድኃኒቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ 5 ሺኅ የሚጠጉ ሰዎች ህይወታቸውን ማትረፍ ተችሏል ያለው ቢቢሲ፤ ከ20 ፅኑ ህሙማን ውስጥ 19ኙ መድኃኒቱን በመጠቀም ከኮሮና ቫይረስ ማገገም ስለመቻላቸውም ብሪታኒያ ተመራማሪዎች ተረጋግጧል ብለዋል።

LEAVE A REPLY