አንጋፋው  የሳይኮሎጂ መምህር ዶ/ር አብርሃም ሁሴን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አንጋፋው  የሳይኮሎጂ መምህር ዶ/ር አብርሃም ሁሴን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዶ/ር አብርሃም በሳይኮሎጂ የትምህርት ፍልስፍና ከፍተኛው ማዕረግ ላይ የደረሱ በበርካታ የጥናትና ምርምር ሥራዎቻቸው የሚታወቁ የሥነ ትምህርት ሙያተኛ ነበሩ።

የባህር ዳር መምህራን ማሰልጠኛን ከመሩ ቀደምት ሙያተኞች አንዱ የሆኑት ዶ/ር አብርሃም በሥርዓተ ትምህርት፣ በትምህርት አስተዳደር፣ በትምህርታዊ ሳይኮሎጂ ዘርፎች በግንባር ቀደምትነት  ከሚጠቀሱ የኢትዮጵያ ሙያተኞች ውስጥ ይመደባሉ፡፡
የባህር ዳር የሥነ ትምህርት ኮሌጅ ዲን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ  ትምህርት ክፍል ሓላፊ ፣ እንዱሁም የሴኔት አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው ዓለም ዐቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባዔዎች በአብዛኛዎቹ ላይ ተካፋይና ቡድኑ መሪም እንደ ነበሩም ተነግሯል።
ዶክተር አብርሃም ሁሴን እስከ ሕይወታቸው ፍፃሜ ባገለገሉበት ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍልን ከማቋቋም እስከ ሓላፊነት አገልግለዋል፡፡  ለሀገርና ለወገን የማጠቅሙ ከ14 በላይ የምርምር ሥራዎችንም አበርክተዋል።
ዶ/ር አብርሃም ሁሴን በቀድሞው የከፍተኛ ትምህርት ኮሚሽን ተቋም  የስኮላርሺፕ ሓላፊ በመሆን ማገልገላቸውን የሕይወት ማህደራቸው  ያስረዳል፡፡ ዕውቁ የሳይኮሎጂ  መምህር  ዶ/ር አብርሀም ስርአተ  ቀብራቸው በሰአሊተ ምህረት  ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY