ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሌተናት ጀነራል መሐመድ ሀምዳን ደጋሉ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አደም መሐመድ አቀባበል አደርገውላቸዋል።
ጀነራሉ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በሁለቱ አገራት የጋራና ሁለትዮሽ ጉዳዮች፣ እንዲሁም በወቅታዊና አፋጣኝ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመከክሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ።