ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ለአምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቻ ከ16 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ንግድ ማጭበርበር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ።
ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል የተለያዩ ዓይነት አዳዲስና አሮጌ አልባሳት፣ የአዋቂና የሕጻናት ጫማዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪዎች፣ የተሸከርካሪ ጎማና መለዋወጫ (ስፔር ፓርት)፣ የምግብ ዘይት፣ ጫት፣ ሀሺሽ እና ልዩ ልዩ ዓይነት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንደሚገኙበት ታውቋል።
በተመሳሳይ በቦሌ፣ በሞጆ እና በአንዳንድ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ በተደረገ ከፍተኛ ቁጥጥርና ፍተሻ ብዛት ያላቸው የንግድ ማጭበርበር እንቅስቃሴዎች ተለይተው በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ሲደረግ፤ 120,000 ሀሰተኛ ዶላርም በሞያሌ ቅርንጫፍ መያዙን ሚኒስቴር መ/ቤቱ ገልጿል።