ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በበርካታ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደረሱ

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በበርካታ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደረሱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ሰሞኑን ያዝ ለቀቅ እያደረገ በመግባባትና  ልዮነት ውስጥ  በሦስቱ  ሀገራት መካከል ሲካሄድ በሰነበተው ድርድር ተሟጋቾቹ  በበርካታ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደርሰዋል ተባለ።

አብዛኞቹ ቴክኒካዊ ጉዳዮች በድርድሩ መፍትሄ እንዳገኙ የገለጸው የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፤ ነገር ግን ለድርድሩ መቋጫ ለማበጀት ሕጋዊ ጉዳዮች ላይ ገና መስማማት የሚያስፈልግባቸው ጉዳዮች አሉ ብሏል።
ይህን በተመለከተም የሀገራቱ የቴክኒክና የሕግ ቡድን አባላት ከሚኒስትሮቹ ስብሰባ በፊት ተጓዳኝ ምክክር ማድረጋቸው እና ይህም ቡድን የደረሰበትን ውጤት ለሦስትዮሹ የሚኒስትሮች ስብሰባ ማቅረቡን መግለጫው ያሳያል።
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን ዘላቂ መብት ለማረጋገጥ የሚደረገው ድርድር ጥንቃቄን ይፈልጋል የሚለው የሚኒስቴሩ መግለጫ፤ ለዚህም ድርድሩ የግብጽና የሱዳን መንግሥታት የሁሉንም አገራት ሉአላዊነትና የጋራ ጥቅም ያከበረ አርቆ ለሚመለከት ዘላቂ ትብብር የበኩላቸውን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አመላክቷል ብሏል።
እልህ አስጨራሽ ነው በተባለለት ዶርድር ላይ ኢትዮጵያ የመርሆች ስምምነትን መሰረት አድርጋ ግድቡን በውሃ የመሙላትና ሥራውን የማካሄድ መብት እንዳላት ግልጽ አድርጋለች።
ኢትዮጵያ ሦስቱም ሀገራት እያደረጉት ካለው በመመሪያዎችና ደንቦች ላይ እያካሄዱት ካለው ድርድር ለሁሉም በሚጠቅም መልኩ ስምምነት ላይ ተደርሶ እንዲጠናቀቅ ጽኑ ፍለጎት እንዳላት የጠቆመው መግለጫ፤
በዚህ ሂደት የሱዳን ተደራዳሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ማነጋገር ስለፈለጉ ፣ ድርድሩ ለአንድ ቀን እንደ ተቋረጠና  የሱዳኑ ውሃ ሚኒስትር ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ማነጋገር ስለፈለጉ ድርድሩ ዛሬም እንደማይኖር አረጋግጧል።
የሱዳን ተደራዳሪዎች ስለድርድሩ ሂደት ከጠቅላይ ሚኒስትራቸው ጋር ለመወያየትና መመሪያ ለመቀበል በመጠየቃቸው የትናንቱ ድርድር ከዚህ በኋላ እንዲካሄድ በስተመጨረሻ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
የሱዳን የሽግግር መንግሥት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌፍተናንት ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸውን ኢትዮጵያ ነገ መዘገቡ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY