ዛሬ ተጨማሪ 195 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ፣ ሀለት ሰዎችም ሕይወታቸው አልፏል

ዛሬ ተጨማሪ 195 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ፣ ሀለት ሰዎችም ሕይወታቸው አልፏል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ  ለ4 ሺኅ 853 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ዘጠና አምስት (195) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺኅ 954 ደርሷል ተባለ።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 44  ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን በውጤቱ አንድም የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም።
ይሁን እንጂ ሁለት በሕምና ማዕከል ውስጥ በሕክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል።
እስካሁን በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሥድሣ አምስት (65) ደርሷል፡፡
በአንጻሩ ትናንት ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች (73 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአማራ ክልል እና 2 ከትግራይ ክልል) ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 934 ደርሷል።

LEAVE A REPLY