ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢ ምቹ፣ ተወዳዳሪና ተመራጭ ለማድረግ እንዲቻል በማቀድ በተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ አማካኝነት ዋና ዋና የሪፎርም ሥራዎች ተካሂደዋል ተባለ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፌስ ቡክ ገጻቸው ዛሬ ባሰፈሩት ጽሑፍ ፤ በዘርፉ ቁልፍ የሕግና የአስተዳደራዊ ለውጦችን ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ከተደረጉት የሕግ ማሻሻያዎች መሀል ዐበይት ሥራዎች ይገኙበታል ሲሉ እንደሚከተለው በዝርዝር አስቀምጠዋል፦
*የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ማሻሻያ አዋጅ 1150-2011 እና ደንብ 461-2012
* በተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ የሚመሰረት የዋስትና መብት አዋጅ 1147/2011 እና ማስፈፀሚያ መመሪያ
* የብድር መረጃ ቋት ማቋቋሚያ መመሪያ ቁጥር CRB-01-2012
* የተጨማሪ እሴት ታክስ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 11572011
* የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1180-2012
* የኢንቨስትመንት አዋጅ ለማስፈፀም የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ
* ኤሌክትሮኒክ ንግድና ግብይት አዋጅ
* አዲስ የንግድ ሕግ (በሚኒስቴሮች ም/ቤት የጸደቀ)
* በውጭ አገራት በተሰጡ የግልግል ዳኝነት ውሳኔዎች እውቅና የመስጠት እና የመፈጸም ስምምነትን ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ ቁጥር 1184-2012
* የግልግል ዳኝነት እና የእርቅ አሰራርን ለመደንገግ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ፤ እንደሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል።