ኢትዮጵያ ዴክሳሜታዞንን ለኮሮና ሕሙማን ለመጠቀም መወሰኗን ገለፀች

ኢትዮጵያ ዴክሳሜታዞንን ለኮሮና ሕሙማን ለመጠቀም መወሰኗን ገለፀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በቅርቡ በብሪታንያ የሕክምና ባለሙያዎች አስተማማኝነቱ የተመሰከረለትና የመጀመሪያው የኮሮና መድኃኒት ሆኖ የተመዘገበው ዴክሳሜታዞንን ኢትዮጵያ በሥራ ላይ ለማዋል መወሰኗን አስታወቀች።

ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድኃኒት እንደ ድንገተኛ ሕክምና ለመጠቀም መወሰኑን  ያረጋገጡት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ናቸው።
መድኃኒቱ የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ 19 ሕሙማን የሕክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት እንደሚሰጥና ተግባር ላይ እንደሚውልም ሚኒስትሯ አስረድተዋል።
መድኃኒቱን በእንግሊዝ መንግሥት የተካሄደው ጥናትና ሪፖርት በዝርዝር ከታየ በኋላ ነው ውሳኔው እንደተላለፈ የተናገሩት፡፡
ከውሳኔው በፊት መድኃኒቱን በተመለከተ የሕክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድንና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት በዝርዝር ተመልክቶታል ያሉት ዶክተር ሊያ ታደሰ፤ ሕክምናውን አስመልክቶ ዝርዝር መመሪያ በቅርቡ ይወጣል  ብለዋል።

LEAVE A REPLY