የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ስለ ዓባይ፣ ኮሮናና ከሊቢያ ጋር ስላለው ጦርነት እንዳይዘግቡ ታገዱ

የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ስለ ዓባይ፣ ኮሮናና ከሊቢያ ጋር ስላለው ጦርነት እንዳይዘግቡ ታገዱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ በሀገሪቱ ስላለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና ከሊቢያ ጋር አገሪቱ እያረገች ስላለው ጦርነት የተመለከተ  ምንም ዓይነት ዘገባ እንዳይሠሩ ታገዱ።

እግዱን ያስተላለፈው የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙኋን ካውንስል መሆኑን ተሰምቷል። በተላለፈው እገዳ መሰረት የግብፅ መገናኛ ብዙኃን እና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መንግሥት ከሚሰጠው መግለጫ ውጭ ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ምንም ዓይነት ዘገባም ሆነ ውይይት እንዲሠሩ አይፈቀድላቸውም።
በሀገሪቱ የኅትመት ሚድያዎች ላይ የሚሠሩ መገናኛ ብዙኃን ይዘቶችን ከማሳተማቸው በፊት ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ማስገምገም እና በጽሑፍ ጥያቄ አቅርበው ፍቃድ ማግኘት እንዳለባቸውም መመሪያው ያዛል።
ግብፅ  እርምጃውን የወሰደችው ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በሚል ሽፋን መሆኑን ሚድል ኢስት አይ ኔት ዘግቧል።

LEAVE A REPLY