ዮናይትድ ኪንግደም ወደ ሀገሯ የሚገቡ መንገደኞችን በክፍያ እመረምራለሁ አለች

ዮናይትድ ኪንግደም ወደ ሀገሯ የሚገቡ መንገደኞችን በክፍያ እመረምራለሁ አለች

A coronavirus diagnostic test kit sits displayed in this arranged photo at the TIB Molbiol Syntheselabor GmbH production facility in Berlin, Germany, on Thursday, March 6, 2020. TIB has reoriented its business toward coronavirus, running its machines through the night and on weekends to make the kits, which sell for about ???160 ($180) apiece. Photographer: Krisztian Bocsi/Bloomberg

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዩናይትድ ኪንግደም ወደ ሀገሯ የሚገቡ መንገደኞችን በክፍያ ልትመርመር ማሰቧን ገለፀች።

ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ መንገደኞች በአየር ማረፊያዎች በክፍያ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማድረግ ከተስማሙ ወደ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ መግባት ግድ ላይሆንባቸው ቢችልም፤ ለምርመራው ግን መንገደኞች 140 ፓውንድ ወይም 170 ዶላር መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ታውቋል።
በቅርቡ ተፈጻሚ ይሆናል በተባለው አማራጭ፤ መንገደኞች የምርመራ ውጤታቸውን በ24 ሰዐታት ውስጥ እንደሚቀበሉ እና የምርመራ ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ በለይቶ ማቆያ መቆየት ግዴታቸው እንደሆነም ተሰምቷል።
የዩኬ መንግሥት ገቢ መንገደኞች ወደ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መወሰኑ ወደ አገሪቱ የሚደረጉ የበረራ ፍላጎቶች እንዲቀንስ አድርጓል ቢባልም፤ ይህንን የመንግሥት ውሳኔ በርካታ የዩኬ አየር መንገዶች ተቃውመውታል።

LEAVE A REPLY