ኢትዮጵያውያን ምሁራን ስለ ህዳሴው ሐሳባቸውን በዓለም መድረክ ሊያቀርቡ ይገባል ተባለ

ኢትዮጵያውያን ምሁራን ስለ ህዳሴው ሐሳባቸውን በዓለም መድረክ ሊያቀርቡ ይገባል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ምሁራን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሳይንሳዊ እና በእውቀት ላይ በተደገፈ ጥናታዊ ሐሳባቸውን ለዓለም ዐቀፍ መድረኮች በማቅረብ ኃፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ።

 የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በታላቁ  የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወቅታዊ ሂደት ዙሪያ ባዘጋጀው መድረክ የተገኙ ምሁራን፤ ግድቡን በተመለከተ እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ ከፍተኛ በመሆኑ በኢትዮጵያም አሁን ያለው መነሳሳት እና ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪያም ከሱዳን ካርቱም፣ በአሜሪካ እና በሌሎች የውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዪኒቨርሲቲ መምህራን በዚህ አንገብጋቢ ወቅት ለህዳሴ ግድቡ ያላቸውን ድጋፍ እና ትብበር እያሳዩ ይገኛሉ ተብሏል።
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፤ የትምህርት እና ስልጠና ማኅበረሰብ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ በሳይንስ የተገፉ ምክረ ሐሳቦችን በማቅረብ የግድቡን ስኬት ከዳር ለማድረስ ከሁሉም አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርትና የሙያ ተቋማት  ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ሞላ ጸጋዬ በበኩላቸው፤ ግብጽ በጉዳዩ ለሌላ አካል ቅሬታ ብታቀርብበትም ሌላኛው አካል በኢትዮጵያ ጫና የመፍጠር ምንም ዓይነት መብት የለውም ብለዋል።
ግብጽ በግድቡ ዙሪያ ኢ-ፍትኃዊ ተግባር እየፈጸመች በመሆኑ ኢትዮጵያ ያላትን እውነት ይዛ ግድቡን መገንባት መቀጠል እንዳለባትና ለዚህ ደግሞ የሁሉም ሚና ከፍተኛ ሊሆን እንደሚገባም ጨምረው አሳስበዋል፡፡

LEAVE A REPLY