ኢትዮጵያ በቢሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ በታሪክ ከፍተኛውን የስንዴ ግዢ ልትፈጽም ነው 

ኢትዮጵያ በቢሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ በታሪክ ከፍተኛውን የስንዴ ግዢ ልትፈጽም ነው 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ ድረስ ከፈጸመችው ግዢ የተለየና በታሪክም ከፍተኛ ነው የተባለለትን የስንዴ ግዢ ልትፈጽም መሆኑ ተነገረ።

እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዮት ከሆነ በአንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር (48 ሚሊዬን ዶላር) 240 ሺኅ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዢ ለመፈጸም የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከአቅራቢ ድርጅቶች ጋር የውል ስምምነት ፈርሟል።
የስንዴ ግዢው ከመደበኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ ስንዴ ግዥ በተጨማሪ ለቀጣዩ በጀት ዓመት ያጋጥማል ተብሎ ለሚጠበቀው የምግብ ዕጥረት እንዲቀርፍ ታስቦ ከፍ ያለ ግዢ እንደሚፈጸም ፌደራል ንብረት ግዢ እና ማስወገድ አገልግሎት አስታውቋል።
በተለይም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ማየሉን ተከትሎ ነገሮች በዚህ መልክ ተባብሰው ከቀጠሉ ብዙኃኑን ኅብረተሰብ መንግሥት ለመደጎም ስለሚገደድ የስንዴ ጭማሪው አስፈላጊና ተገቢ ነው ተብሎለታል።

LEAVE A REPLY