የመጀመሪያው የኮሮና ክትባት በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ ነው

የመጀመሪያው የኮሮና ክትባት በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ክትባት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሊካሄድ እንደሆነ ተሰማ።

ደቡብ አፍሪካ ለዚህ የክትባት ሙከራ የተመረጠችው ከአፍሪካ በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ያሉባትና ወረርሽኙም በፍጥነት እየተስፋፋባት ከመሆኑ ባሻገር ሙከራውን በ ትክክል ለመተግበር የሚያስችሉ በርካታ የሕክምና ባለሙያዎች የሚገኙባት ስለሆነችም ጭምር ነው ተብሏል።
የክትባት ሙከራው ኦኤክስ1ኮቪድ- የኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ሳርስ-ኮቪ-2 የተባለውን ቫይረስ እንዳይያዙ ለመከላከል የታለመ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ የሚደረገው ይህ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ የዊትስ ዩኒቨርስቲ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እና ኦክስፎርድ ጀነር ኢነስቲቲዩት ከተባሉ ተቋማት ጋር የሚካሄድ እንደሆነም ተነግሯል።

LEAVE A REPLY