ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ሰለማዊ በሆነ መንገድ በጋራ ሊሠሩ ይገባል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በድጋሚ አሳሰበ።
የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቴፋን ጃሪክ ሀገራቱ በግድቡ ግንባታ ዙሪያ ያላቸውን ልዩነት ዘላቂ መፍትኄ ለመስጠት በልዩነቶቻቸው ላይ በጋራ መምከር ይጠበቅባቸዋል ሲሉ መክረዋል።
ቃል አቃባዩ ሀገራቱ እ.ኤ.አ. በ2015 በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያላቸውን ልዩነቶች ዓለም ዐቀፍ ሕጎችን መሰረት በማድረግና የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ ሁኔታ፤ በትብብር መንፈስ ለመፍታት ያስቀመጡትን መርህ በመከተል ለችግሮቻቸው እልባት ማበጀት እንደሚገባቸው ማሳሰባቸውን ሲጂ ቲ ኤን ዘግቧል።