ኃይሌ ገብረ ሥላሴ  በኮሮና ምክንያት 200 ሚሊዮን ብር ከሰረ

ኃይሌ ገብረ ሥላሴ  በኮሮና ምክንያት 200 ሚሊዮን ብር ከሰረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ኢትዮጵያዊው አትሌትና ኢንቬስተር ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በኢትዮጵያ የከፈተው ግዙፉ ሀዮንዳይ የመኪና ካምፓኒ ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርጎብኛል አለ።

እንደ ኃይሌ ገለጻ ከሆነ የኮቪድ-19 በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ በኢትዮጵያ የሃዩንዳይ ተሽከርካሪዎች አስመጪ እና መገጣጠሚያ ኩባንያው ማራቶን ሞተርስ 200 ሚሊዮን ብር አጥቷል።
ሥራ ከጀመረበት አጭር ጊዜ ውስጥ ስኬታማ መሆን የቻለውና ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈላጊነትን መቆናጠጥ የቻለው ሀዮንዳይ የመኪና መገጣጠሚያ ቀደም ሲል ከተገነባውና መገናኛ ጫፍ ይገኝ የነበረው ትልቅ ህንፃ ወጥቶ ላም በረት ከሚባለው ሥፍራ “ማራቶን ሞተርስ” የተሰኘ ግዙፍ ህንፃ መገንባት ችሏል።
 የማራቶን ሞተርስ ባለቤት የሆነው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ከትንሽ እስከ ትልቅ የሚባሉ የንግድ ተቋማት ገቢያቸው እያሽቆለቆለ እንደሚገኝ ጠቁሞ፤ የእርሱ ካምፓኒ የሆነው ማራቶን ሞተር ኢንጅነሪንግም ኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ከተገኘበት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ፣ አስካሁን 200 ሚሊዮን ብር ገቢ አጥቷል ሲል ተናግሯል።

LEAVE A REPLY